WAO- We All One! Ethiopians!

WAO- We All One! Ethiopians!

Monday, July 6, 2015

The Lion Of The Lions! የአንበሶች አንበሳ!! መጣ እያገሳ!

አንበሶች አንበሳ!
ኢትዮጵያን አለ መጣ ተነሳ፡፡
ኢትዮጵያ ወይም ሞት ብሎ ፎከረ፣
ጠርጎ እየመታ እየሰበረ፣
እየገፋ ነው ብሎ ወደፊት፣
ድልን አግኝቶ እስኪያይ ነፃነት!
 

The Lion Is Watching! አንበሳው እያየ ነው! ዋ!ዋ!ዋ!

አንበሳው ያያል ጠላት ይጭነቀው፣
ሻቢያ ወያኔውን ጠርጎ ሊያጠፋው፣
ኢትዮጵያን ሊያስከብር እንደ ለመደው፡፡

እንደ ንጉሣችን ኢትዮጵያ ወይንም ሞት! አንድነት የግድ ነው በማለት በህብረት! በዓለም እንነሳ በአራቱ ማዕዘናት!

all pictures 042.jpgበዓለም ተበትነን በወሬ ስካር
ምንም ለማይገኝ አንጎል ከማዞር
ጥርስን ነክስ አርገን ስልቱን እንቀይር
እንደ አያት ቅድመ አያት በመሆን ድፋር
እውነተኛ ሁነን  እንቁም ለአገር
ኢትዮጵያ ወይም ሞት ብለን እናምርር
ነፃነት ለማግኘት ያለጥርጥር፡፡

Sunday, July 5, 2015

One Flag! One People! Ethiopia! አንድ ሰንደቅ ዓላማ! አንድ ሕዝብ! ኢትዮጵያ! አክራሪነትን በሁሉም አይነት እንዋጋ! በመከባበር! ሐይማኖት የግል ነው፤ አገር የጋራ ነው የሚለውን መሪ ቃል እንቀበል! ኢትዮጵያውያን በጣም ልዩ መሆናችንንና በምነታችን ችግርም እንደሌለብን ዓለም ያውቃል።

                                   ሰንደቃላማችን
ልዩ መለያችን፡፡
የጥቁር ሕዝብ ተስፋ
ጠላትን ወራሪን አሳዶ የደፋ
እንደ ሚቻል ሁሉ ያሳየው በይፋ፡፡
ኢትዮጵያውይ ሁሉ በዓለም አውለብልበው
ቀንዳሙን አጥፋና ክልሉን ስበረው፡፡

Saturday, July 4, 2015

ምርጡና ቆራጡ የእነ አጅሬ ዘር፣ ኢትዮጵያን እያጣህ ከምትቸገር፣ ጠላትህን ምታ ውጋና ወርውር!

ከኢትዮጵያ ከእናቱ ከአገር ከቀየው፣
ውሀውም ደርቆበት ቀኑም ጨልሞበት የሚሰቃየው፣
ኢትዮጵያውይ ወገን  ጀግናው፣ ጀግናው፡፣
ድምፅህን ጠፋ አርገህ እጅህን አያይዘህ ጠላትን ግፋው፣
ይህ ነው መንገዱ ለድል ሚያበቃው!

እየተሰቃየህ በርሀብ ከምትሞት!ኢትዮጵያዊ ሸፍት! ያለዚያ ባዶ ነው ዝም ብለው ቢያዩት! ድምፅ አጥፋ ወድር! ጠላት እንዲጨንቀው እንዲደናበር!!!

ስላም በዓለም አቀፍ ዙሪያ ያላችሁ የአጊላ ኢትዮጵያ ተፋላሚዎችና ደጋፊዎች በሙሉ፦እንደምን አላችሁ? በዛሬው ለት 3:30 አካባቢ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ 95 ኪሎ ሜትር ርቃ ከምትገኝ ከተማ ደውየ የኑሮውን  ሁኔታ ጠይቄ የተረዳሁትን ይኽው ላካፍላችሁ።
1 አንድ ኩንታል ጤፍ $2000.00
2.አንድ ኪሎ በርበሬ $150.00
3. አንድ ኪሎ ቅቤ   $220.00
4. አንድ ኪሎ ነጭ ሽንኩርት $85.00
5. አንድ ኪሎ ምስር  $58.00 …ወዘተ  የኢትዮጵያ ሕዝብ ያለበትን እሳት ለአገርና ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያስብ ሁሉ በሀይል ሊያቃጥለው ይገባል፡፡ እስከመቼ!የኢትዮጵያ ሕዝብ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ይቀጥላል!!!
  

Saturday, June 6, 2015

ኢትዮጵያ እሺ በላይ ዘለቀዎችን ትሻለች!



The PhoTo of Belay Zeleke.GIF
ወያኔ ተኩላው አጫጭር አንገት፣
ፍጹም የተሳነህ አዙረህ ማየት፣
ጀግና እየመጣ ነው ሊያነድህ በእሳት፣
አንቀጽ አያድንህ ሰላሳ ዘጠኝ፣
ከምኒሊክ ግቢ እያልህ አስጥሉኝ።
እንደ ተጻፈው እንደ አለው ትንቢት፣
መሄጃም አታገኝ ከዚያው ነው ምትሞት።























Sunday, May 10, 2015

አባቶችማ ነቅተውና ጠብቀው፤ እኛን ግን አስማረኩ ትምህርት ቤት ልከው!

It was at the Battle of Adwa that King Menelik II of Ethiopia defeated ...




                                                                                                               

እኛ ጠብቀን አስረከብናችሁ
እናንተ ግን ተሞኛችሁ።                                                                    
አወቅን ብላችሁ ሳታውቁ፣
ይኽው ታያችሁ ስታልቁ።
የመጀመሪያ የነበራችሁ፣
ምነው በጣም የቀራችሁ።
 በሀይል! ፈትሹ መርምሩ፣
ስለ እራሳችሁም ተማሩ፣
እወቁ በማን እንደ ምትመሩ፣
ወደ አገራችሁም ቆርጣችሁ ዙሩ፣
ይብቃ ብላችሁ በዓለም መዞሩ፣
በሀይልም ኢትዮጵያን አስከብሩ፣
ኮርታቹሁ ለዘለላለም እንድትኖሩ።
             

Tuesday, May 5, 2015

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውይነት በመንታ ጠላቶች በቀኝም በግራም ሲጠቃ ዝም ብለን አንመልከት!

      
Logo.png
    አረባዊ አክራሪነት በኢትዮጵያውን የእስልምና አማኞች ላይ የዘርጋው ወጥመድ፤ በአፋጣኝ ከአልተገታ ውጤቱ በጣም የከፋ ነው። ሰላማዊ የኢትዮጵያ እስላሞች፦በዘረኞች የአርቦች ቅስቀሳ፤ ከኢትዮጵያውይነት እያወጡ በአክራሪ አረቦች እየተመሩ በፀረ ጥቁርነት እየተሞሉ መሆኑን ኢትዮጵያውይ ዜጋ ሁሉ በሀይል ሊገነዘበው ይገባል።በመጤው ሐይማኖት መስመጥና የራስን የነበረን መልቀቅ፤ መጨረሻው ፀፀት ይሆናል።
አክራሪ አረቦች በሳውዲ አረቢያ ጠይም የኢትዮጵያን እስላሞች ምን ያህል እንደ ሚያሰቃዩ የሚያውቅ ሁሉ በጣም ልብ የሚነካ መሆኑን ይገነዘባል። ስለዚህ፦ ኢትዮጵያውይ ሁሉ  መንቃት፣መገንዘብና ማወቅ አለበት።
  ኢትዮጵያን መውደድና እግዚአብሄርን ማምለክ አንድ ነው! እግዚአብሄርን መውደድና ኢትዮጵያን ማምለክም አንድ ነው። አንዱ በሌላው ይገለፃልና! ሁለቱም ስለ ፍቅር ናቸውና!
               ኢትዮጵያን ውደዱ፣
               ለመጤ አትስገዱ፣
               የጥንቱን የቢላል፤ ፈለጉን ውሰዱ፣
               ኢትዮጵያን አትክዱ፣
               እንደ አትዋረዱ
               ኢትዮጵያን የካዱ፣
               ቀሩ እንደ ነደዱ፣
              በዓለም እየዞሩ የትም እየሄዱ።
              ስለዚህ፦ የሞከረ ሁሉ ኢትዮጵያን ሊያጠፋ፣
                          ገና ሳይጀምረው ወዲያው ነው ሚደፋ።
                          ከቅርብ እንጀምር በመለስ አይተናል፣
                          ሳዳም በገመድ በአየር ላይ ተሰቅሏል፣
                          ሞባረክ በአመፅ ትንፋሹ ተቕርጧል፣
                           ጋዳፊም መሬት ላይ እንዲያ ተንከባሏል፣
                           ሻቢያም በማቀብ ታስሮ ተወጥሯል።
                           አወ! የኢትዮጵያን ጠላቶች፣
                            አምላክ ይመታል አንድ በአንድ የሷ ተሟጋች!
                             
              
              
             
        

Monday, May 4, 2015

አሜሪካ አይሲስን ለምን ፈጠረችው? ክንፉ አሰፋ

 ግብጽ የሃያ አንድ ክርስቲያን ዜጎችዋን በአይሲስ መታረድ ዜና እንደሰማች ዝም ብላ አልተቀመጠችም ነበር። ብሄራዊ የሃዘን ቀንም አላወጀችም። እንዲህ ነበር የሆነው። ከመቅጽበት ተዋጊ አውሮፕላኖችዋን አስነስታ ወደ ሊቢያ ላከቻቸው። የአይሲስ አራጆች የተከማቹበትን ደርና የተሰኘ ስፍራ እያከታተለች በቦምብ ቀጠቀጠችው። ብዙ አራጆች በድብደባው አለቁ። እንደ ግብጽ አጀማመር ቢሆን የሊብያው አይሲስ ክንፍ ድሮ-ድሮ ከምድረ-ገጽ ይጠፋ ነበር። ግና አልሆነም። አሜሪካ ጣልቃ ገባች። ግብጽ የአሜሪካን “ጸረ-ሽብር” ዘመቻ በማገዝዋ ምስጋና ማግኘት ሲገባት በተቃራኒው ተወገዘች። ከጥቂት ድብደባ በኋላ ፔንታጎን ግብጽን አስጠነቀቀ[0]። የኦባማ አተዳደርም ደብደባው በአፋጣኝ እንዲቆም ቀጭን መልእክት ላከ። ይህ ድርጊት ከዚህ ቀደም ስለ አይሲስ አፈጣጠር ኤድዋርድ ስኖደን[1] የለቀቀው ምስጢራዊ መረጃ ጋር ተዳምሮ በአሜሪካ ላይ የነበረውን ጥርጣሬው አጠናከረው። ነገሩን ለማመን ያዳግት ይሆናል። በግልጽ የሚታዩ መረጃ እና ማስረጃዎች ግን ተአማኒነታቸው ጥርጥር ውስጥ የሚገባ አይደለም። “በአይሲስ እየታረዱ ያሉት ዜጎች የፊልም ቅንበር እንጂ እውነት አይደለም![2]” የሚሉ ባለሞያዎችም የትንተናቸው መነሻ ከዚህ ጉዳይ ጋር ይያያዛል። ይህ አሸባሪ ድርጅት ስራውን ከጀመረ አንድ አመት ባልሞላ ግዜ ውስጥ ከመቶ ሺ በላይ ዜጎችን በአሰቃቂ ሁኔታ እንደገደለ ይናገራል። ቦምብ እንደዝናብ የሚወርድባቸው ሃገሮች፤ ሶማልያ፣ የመን፣ ኢራቅ፣ ሶርያ፣ አፍጋኒስታን፣ፓኪስታን… ተደምረው አይሲስ ከሚነግረን ግድያ ሩብ ያህሉንም አላደረጉም። የሃያላን ሃገሮች ምላሽ ግን በአፍ ከማውገዝ ያለፈ አለመሆኑ በአይሲስ አሰራር ላይ ተጨማሪ ጥርጣሬ ይፈጥራል። አይሲስ የእስራኤል፣ የኢንግሊዝ እና አሜሪካ የጋራ ፕሮጀክት መሆንን ያጋለጠውን፤ የኤድዋርድ ስኖደን መረጃ እንደገና እንድንመረምረው ይገፋናል። በአይሲስ ዙርያ የሚተነትኑ አንዳንድ ጸሃፊዎች እጃቸውን በአሜሪካ ላይ መቀሰር ከጀመሩ ሰነበትበት ብለዋል። አሸባሪ ሃይልን መፍጠር ለአሜሪካ የመጀመርያ አይደለም። አላማው ይለያይ እንጂ ኦሳማ ቢን ላደንም የአሜሪካ ስሪት መሆኑ በይፋ ተገልጿል። የአሜሪካ ቁጥር አንድ ጠላት የነበረው ኦሳማ ቢን ላደን በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት በአሜሪካው የስለላ ተቋም፤ በሲ.አይ.ኤ እንደተፈጠረ በግልጽ ተቀምጧል። እ.ኤ.አ. በ1979 ሶቭየት ህብረት አፍጋኒስታንን በወረረች ግዜ ኦሳማ ቢን ላደን አማጺውን የሙጃህዲን ሃይል በመቀላቀል ወደ አፍጋኒስታን አመራ። በወቅቱ አሜሪካ ሙጃህዲንን ለማሰልጠን እና ለማስታጠቅ ሶስት ቢሊየን ዶላር እንዳፈሰሰች የብሪታንያው ዜና አገልግሎት ቢ.ቢ.ሲ. ዘግቧል። እንደ ቢ.ቢ.ሲ. ዘገባ ሲ.አይ.ኤ. ለኦሳማ ቢን ላደን በግል ደረጃውን የጠበቀ የኢንተልጀንስ ስልጠናም አድርጎለታል። ቀዝቃዛው ጦርነት ሲያበቃ እና ሶቭየት ህብረት አፍጋኒስታንን ለቅቃ ስትወጣ ነው ቢን ላደን አሜሪካ ላይ የዞረው። የዘመናችን ዘግናኝ የሽብር ድርጅት የሆነው አይሲስንም የፈጠረችው አሜሪካ ናት የሚሉ ጸሃፍት ጥቂት አይደሉም። የእነዚህ ተንታኞች መረጃ በከፊል የሚንተራሰው ከአሜሪካ ብሄራዊ ደህንነት ኤጀንሲ ሰነድ የጠለፈው ኤድዋርድ ስኖደንን ነው። የአሜሪካ ስለላ ድርጅት NSA ውስጥ ይሰራ የነበረው ይህ ሰው የአሜሪካን ብሄራዊ ምስጢሮች ካጋለጠ በኋላ ሩስያ ውስጥ ተደብቋል። እርግጥ ነው። ኤድዋርድ ስኖደን የለቀቀው ሰነድ የአይሲስን አፈጣጠር ምስጢር በጥቁርና – ነጭ አስቀምጦታል። ሾልኮ የወጣው ይህ ሰነድ የአይሲሱ መሪ አቡባክር አል ባግዳዲ የአሜሪካ ደህንነት ግብአት እንደሆነ ይገልጻል። እንደ ምስጢራዊው የኬብል መረጃ ከሆነ ለአይሲስ መመስረት ሃላፊነቱን የሚወስዱት እስራኤል፣ ታላቋ ብሪታንያ እና አሜሪካ ናቸው። “ምክንያቱም” ይላሉ ዶክመንቱን የሚተነትኑ አምደኞች፣”ምክንያቱም እስላማዊ ጦረኞች የሚሏቸው ሃይሎች ሁሉ ከአለም ዙርያ እየሄዱ ሶርያ ላይ እንዲሰባሰቡ ነው።” ይህ ስትራቴጂ እውን ሲሆን፤ በአንድ በኩል በእነሱ የሚመራ ህይል ለማስቀመጥ እና በሌላ በኩል ደግሞ እስራኤል በቅርብ አደጋ ላይ መውደቋን ለማስመሰል የተወጠነ ታክቲክ ነው። መካከለኛው ምስራቅ ሽብር ያለ ማስመሰሉ አካባቢውን ዘልቆ ለመቆጣጠር ይረዳቸዋል። ይህን ለማድረግ አይሲስን እንደ ምክንያት ይጠቀሙበታል።” የኤድዋርድ ስኖደን ምስጢራዊ መረጃ በጥሬው ተቀብለን፣ ስነዱን እንደማስረጃ ወስደን ለድምዳሜ መቸኮል የለብንም። ጉዳዩ ትንሽ ከበድ ያለ ነውና ሌሎች ተጓዳኝ ነገሮችን መመርመርም ተገቢ ይሆናል። የእስላማዊ ዲሞክራቲክ ጂሃድ ፓርቲ መስራች እና ቀደም ሲል ከፍተኛ የአልቃይዳ ኮማንደር የነበረው ናቢል ናኢም ለሜዲያ የተናገረው መረጃ የኤድዋርድ ስኖደንን ማስረጃ ያጠናክረዋል። ናቢል ናኢም ለቤይርቱ ፓን አረብ ቴሌቭዥን በሰጠው ቃል፤ “አይሲስን ጨምሮ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያላቸው ደርጅቶች ሁሉ፤ በአሁን ሰዓት እየሰሩ ያሉት ለአሜሪካው የስለላ ተቋም ለሲ.አይ.ኤ. ነው።” ሲል በዚህ ወር መግቢያ ላይ ተናግሯል[3]። ናቢል ናኢም በቴሌቭዥን የሰጠው አስደንጋጭ ምስጢር በዚህ አላበቃም፤ ሌላም ለማመን የሚከብድ ነገር አክሎበታል። አይሲስ በደንብ የሰለጠነ እና በደንብ የታጠቀ የሽብር ድርጅት ነው። መጠነ ስፊ የሆኑ የኢራቅን እና የሶርያን ክልሎች ተቆጣጥሯል። የባህሬኑ “ዘ ገልፍ ዴይሊ ኒውስ” ጋዜጣም ባለፈው አመት አጋማሽ ላይ በዋና ገጹ የአይ.ሲስ መሪ አቡ ባክር አል ባግዳዲን የእስራኤሉ የስለላ ድርጅት ሞሳድ በጦር፣ በመንፈሳዊ ትምህርት እና በንግግር ክህሎት እንዳሰለጠነው ጽፏል[4]። የዮርዳኖስ ባለስልጣናትን ጠቅሶ “ወርልድ ኔት ዴይሊ” የተሰኘው ጋዜጣ የአሜሪካ ወታደሮች በዮርዳኖስ ግዛት ውስጥ የአይሲስ አባላትን እንዳሰለጠኑ ዘግቧል[5]። እነዚህን መረጃዎች በአንድ ወገን እንያዛቸው እና ወደ ሌሎች ምልከታዎች ደግሞ እንሂድ። ታላላቅ የአሜሪካ ጋዜጠኞችም የአይሲስ መጠናከር እና የአለም ዝምታ እንቆቅልሽ ነው የሆነባቸው። የፎክስ ኒውስ አምደኛ የሆነችው ግሬታ ቫን ሱስተረን እንግዳ የሆነባትን አስደንጋጭ የአይሲስ ግድያ እና የምእራባውያን ዝምታ እጅግ በመደነቅ ታነሳለች። አይሲስ በሺዎች የሚጠጉ ክርስቲያኖችን እያረደ፤ የተባበሩት መንግስታት፣ አሜሪካም ሆነ የአውሮፓ ህብረት ጉዳዩን ከምንም አልቆጠረውም ብላለች። ጋዜጠኛ ግሬታ ንግግርዋን ቀጠለች። “ያለነው በሂትለር ዘመን አይደለም። ዘመኑ የመረጃ ነው። እልቂቱን የሚያሳዩ መረጃዎች በግልጽ ይታያሉ። አሰቃቂ መረጃዎችን እየተመለከተ አለም ግን ዝም ነው ያለው። ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ሊጋባን በማይችል ምክንያት ጉዳዩን ችላ ብሎታል። …” ትላለች። ሌላው ሉ ዶብስ የተባለ በአሜሪካ ታዋቂ የቴሌቭዥን አቅራቢና ጸሃፊ፤ ህዝብ እየታረደ አለም ግን በአይሲስ ላይ ችላ ማለቱ እንዳስገረመው ይናገራል። ጋዜጠኛ ሉ ዶብስ ሜሪካዊውን ደራሲ ጆኒ ሞር በጉዳዩ ማብራርያ እንዲሰጥም አድሮታል። ጆኒ ሞር “Defying ISIS” “ውጉዝ መአሪዮስ አይሲስ” የሚል መጽሃፉ አይሲስን ከናዚዎች ጋር እያመሳሰለ ነው ያስቀመጠው። ጆኒ ሞር በፎክስ ኒውስ ላይ ቀርቦ የተናገረው ያስደምማል። “የ አይሲስ አራጆችን የጫኑ አርባ መኪናዎች በአንዲት የሶሪያ መንደር በነጻነት እየተዘዋወሩ 3000 ክርስቲያኖችን አፍሰው ወሰዱ። … ቦስንያ ላይ በቀን 140 ቦምብ ሲጥሉ የነበሩ የኔቶ ተዋጊ አውሮፕላኖች፣ በኢራቅ እና ሶርያ ላይ በቀን ከ 7 – 12 ቦምብ ሲጣል አይሲስ ግን ችላ ነው የተባለው።” ጆን ዊልገር የተሰኘ የፖለቲካ ተንታኝ ደግሞ በአንድ ጥናታዊ ጽሁፉ፤ “አይሲስ የአሜሪካ ፍጡር ነው” ከማለት አልፎ፣ አይሲስን ከካምቦዲያው ካመሩዥ ጋር ያመሳስለዋል። በ 1969 እ.ኤ.አ. ፕሬዝዳንት ኒክሰን ካምቦዲያን በቦንብ አስደብድበው ሲያበቁ አንባገነኑ ፖል ፖትን አበቀሉ። የፖልፖት ካመሩዥ ከአይሲስ ጋር የሚያመሳስላቸው ነገር አለ። “ሁለቱም የአሜሪካ ውጤቶች፣ ሁለቱም የጨለማው ዘመን ጨካኞች ናቸው” ሲል ጽፏል። ይህን ክስተት ስከታተል “ሲ. አይ. ኤ – ዘ ከልት ኦፍ ኢንተሊጀንስ” የተሰኘው መጽሃፍ ታወሰኝ። ቪክቶር ማርቼቲ የተባለ የቀድሞ ሲ.አይ.ኤ አባል የጻፈው “ዘ ከልት ኦፍ ኢንተሊጀንስ” መጽሃፍ አሚሪካኖች ብሄራዊ ጥቅማቸውን ለማስከበር የማያደርጉት ነገር እንደሌለ ይነግረናል። ሲ. አይ.ኤ. የአሜሪካን ብሄራዊ ጥቅም ሲያስከብር ለሞራል እሴቶች፣ ለሰዎች ስብዕና እና ለፍትህ ቦታ እንደማይሰጥ ደራሲው ቪክቶር ማርቼቲ ይነግረናል። መጽሃፉ በከፊል በአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሳንሱር ተደርጎ የወጣ ነው። እንደዚህም ሆኖ ሲ.አይ.ኤ. ከረቀቀ ቴክኖሎጂ እስከ ረቀቀ ወንጀል እንደሚሰራ ይተነትናል። አሜሪካኖች ጉዳያቸውን ለማስፈጸም ዝናብ ማዘነብ ካለባቸው እንኳን፤ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ያንን ሊያደርጉ እንደሚችሉ መጽሃፉ ያሳየናል። የአይሲስ አራጆች የሚናገሩት እንግሊዝኛ በአሜሪካ ቅላጼ (አክሰንት) ነው። አሜሪካ ተወልደው ያደጉ ሽብርተኞች ሊሆኑ ይችላሉ ብለን እንውሰድ። አይሲስ የሚለቅቃቸውን የቪድዮ ምስሎች የሚጠራጠሩ ባለሙያዎች፤ ጉዳዩን ከፖለቲካ ብቻ ሳይሆን ከሙያ አንጻርም ይመለከቱታል። የጃፓን ዜጎች ሲታረዱ የሚያሳየውን ቪድዮ ፍሬም፣ በፍሬም እያሳዩ የአይሲስ ግድያ ውሸት መሆኑን ለመግለጽ የሚሞክሩ የፊልም ባለሞያዎች የሚናገሩት ሙሉ በሙሉ ባያሳምንም ተመልካቹን ማደናገሩ አልቀረም[6]።

የአሜሪካ የውጪ ፖሊሲ የድንቁርና መግለጫ ወይንስ የፅንፈኝነት እብሪት::

                                                ሚያዝያ 13/2007 April 21/2015                                                             አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ስለምዕራባውያን ያለን አመለካከት በእጅጉ እየተለወጠ የመጣው በወያኔ ዘመን ነው:: ምዕራባውያን ብለን የምንጠራቸው አገሮች ከመርህ ተነስተው በዲሞክራሲ የሚሰጡት ስፍራ አለ ብሎ በማጋነን ያየው የነበረው እይታው የተለወጠው የትግሬ/ወያኔ አገዛዝ ስልጣን ላይ ቁጢጥ ካለበት ጊዜ ወዲህ ነው:: ምንም እንኳን የቀዘቃዛው ጦርነት ተብሎ ይጠራ በነበረበት ዘመን በጥቂቱ ከ30 ዓመቶች በፊት ምዕራባውያን ሰው በላ የሆኑ መሪዎችን አቅፈውና፣ ደግፈው፣ አሞካሽተው እሽሩሩ ይሏቸው እንደነበር የቅርብ ትዝታ ቢሆንም፣ እንደአሁኑ ዘመን በተለይም አሜሪካ አለም አቀፋዊ እይታዋ ይህን በመሰለ ሁኔታ ይለወጣል የሚል ግምት በማንኛችንም ግምት ውስጥ አልነበረም:: ከሶቭየት ሕብረት መውደቅ በፊት በፀረ ኰሚኒዚም አባዜ የተተበተበው ፖሊሲ ወደ ፀረ ሽብርተኝነት ምትሃታዊ ቅዠት ከተለወጠ ወዲህ ዓለምን የሚጋልበው አንድና ብቸኛ ሃያል ሆኗል:: የአሜሪካ የውጪ ፖሊሲ ከአገሮች ጋር ቅራኔ ገብቷል:: የአሜሪካ ብሔራዊ ጥቅም ከሕዝብ መብትና ጥቅም፣ ከአገር ሕልውና በላይ ሆኗል:: በምዕራባውያን አገሮች መካከል በተለይም በአፍሪካ የመልካም አስተዳደር እና የዲሞክራሲያዊ ስርአት መስፋፋትን ትኩረት ሰጥተንበታል በሚል ሽፋን በሎሌ መሪዎች አማካይነት በመፈፀም ላይ ያሉ ደባዎች የአገራችንን ችግር ውስብስብ በሆኑ ሰንሰለቶች እያቆላለፉት መጥተዋል:: የአሜሪካ ወታደራዊ ጀብደኝነት ያስከተለው መዘዝ አላማችንን ወደ አልተረጋጋ ሁኔታ ወስዷታል:: በአሜሪካ በኩል ሃይልን ጨምሮ የመራመድ ፅንፈኛ አቅጣጫ አለምን በምስሏ ለመቀረፅ ከምታደርገው ምኞቷ ጋር የተያያዘ ነው:: ይህ ፅንፈኛና ብቸኛ ልዕለ ሃያል ሆኖ መገኘት ያስከተለው ጀብደኝነት ሰብአዊ ፍጥረት ለሆነው ሁሉ የሕሊና ቁስል እየሆነ መጥቷል:: ከቀድሞዋ ከሶቭየት ሕብረት መፍረስ በፊት አሜሪካኖች በነበራቸው የፀረ ኰሚዩኒዝም ትግል ሳቢያ፣ ከትቢያ ያነሷቸውን የፀረ ኢትዮጵያ ቡድኖች ወያኔና ሻቢያን አቀላምጠው በመያዝ ለሥልጣን ካበቋቸው ወዲህ በኢትዮጵያ ሕዝብ ህልውና ላይ ደባ እየተፈፀመባት ይገኛል:: አለአሜሪካኖች ድጋፍ እንደማይኖር የተረዳው ወያኔ የታዘዘውን በመፈፀም ተላላኪ መሆኑን በማረጋገጡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በህይወቱ ዋጋ እየከፈለበት ነው:: ምዕራባውያን ይህን የዘመናችንን ሎሌና ተላላኪ አገዛዝ በመዳፋቸው ውስጥ የገባ እያለ ሌላ አማራጭ ያስባሉ ወይንም በዲሞክራሲ መስፈርት ይመራሉ ብሎ ለመገመት የማይቻልበት ወቅት ተደርሷል:: ከአክራሪ ኰሚንስትነት ከመቀፅፈት ወደሎሌነትና የነሬገንን ኒኦ-ኰንሰርቫቲዝም አክራሪ ፖሊሲ ቡራኬ የተቀበለው የአንድ የዘር ቡድን ስልጣን ከመያዙ በፊት ጀምሮ በውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ላይ ተፅእኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ጋዜጠኞ፣ ታዋቂ ሰዎች፣ ፖለቲከኞችን በወዳጆቻቸውና በሎቢ (Lobby) ኩባንያዎች በኩል ያጠናቀቁት ሽርክና ስለነበር ዛሬ በመንግሥት ስልጣን ባለቤትነቱ በእጁ ያስገባው ሃብት ለድለላ እና ለሽንገላ እንዳሻው ለመጠቀም ሁኔታው በመፍቀዱ የተቃዋሚ ድርጅቶች ድምፅ ባዶ ሜዳ ላይ እየወደቀ መጥቷል:: 2 እኛ ኢትዮጵያኖች ምዕራባውያን በተቀዳሚ አሜሪካኖች በኢትዮጵያ የሚደረገው የዲሞክራሲ ትግል በፍትሐዊነት የሚጠናቀቁበት ሁኔታ ይደግፉ ይሆናል ብለን ማሰብ ሳይሆን፣ በምን ዓይነት የመራራ ትግል ወደፈለግነው ግብ ለመድረስ በሚከፈለው መስዋዕትነት ዙሪያ ትኩረት መሰጠት እንዳለበት ግንዛቤዎችን ካገኘን ብዙ ዓመቶችን አስቆጥረናል:: የወያኔ ወዳጆችና አሽቃባጮቻቸው ለፍትሃዊ ፍለጋ የሚደረገውን መራራ ትግል እንዲታያቸው፣ በመጪው ዘመን የተበደለ ሕዝብ የምስራች የሚበሰርበት መሆኑን ለማስገንዘብ እየዳህን ካለንበት የትግል ጉዞ መነሳት ይኖርብናል:: ፍትሃዊ አማራጭ በልመና አይመጣም፣ አሜሪካኖች ጋዜጣዊ መግለጫ አይሻርም፣ ፍትሃዊ ጥቅማችንን በእጃችን ውስጥ የምናስገባው ወያኔን የሚደግፉትን ስትራቴጅካዊ ጥቅማቸው ጋር ስንጋጭ ነው:: ይህን ሲያዩ ለመፍትሔ ፍለጋ፣ ለድርድር ይጣደፋሉ:: አሜሪካኖች የሚደግፉት አገዛዝ ቁመናው አሳፋሪ፣ ባህሪውም ጋጠ ወጥ፣ ዘረኛ አገዛዝ መሆኑን ያውቁታል:: ለውጪ መንግሥታት አቤቱታ የሚያቀርብ፣ ማመልከቻ ይዞ የሚንከራተት፣በአውሮፓ መንገዶች የሰላማዊ ሰልፍ ጩኀት ብቻውን ምዕራባውያን ከስትራቴጂካዊ ጥቅሞቻቸው አንፃር የያዙትን መሞዳሞድ አንዳችም ስንዝር ፈቀቅ አያደርጋቸውም:: ከዚህ በላይ መጠናቀቅ ያለባቸው ጉዳዬዎች እንዳሉ ኢትዮጵያዊነት ጠንቀቆ ያውቃል:: በኢትዮጵያና በሕዝቧ ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ብሎም ችግሮችን ለማስወገድ ክብራችንንና ነፃነታችንን ለማስከበር ለምንወስደው እርምጃ የማንንም መንግሥታት እውቅና አንጠብቅም:: በትግሬ/ወያኔ አገዛዝ መዘዝ ምክንያት ሉዓላዊነቷ ከተተበተበበት ችግር በማላቀቅ ለሕልውናችን የሚያስፈልገውን ሰላምና ብልፅግና ለዚህ ደግሞ በመሣሪያነት እጅግ ፍቱን የሆነው የዲሞክራሲ፣ የመብትና የሕግ የበላይነትን ጥያቄ በአስተማማኝ ሁኔታ በአገራችን የሚዘረጋበትን ሁኔታ ለመፍጠር ሐላፊነቱን በዜጐቿ እጅ ላይ የወደቀ ነው:: ላለፉት 24 ዓመታት በአገራችን ኢትዮጵያ አገዛዙ በስልጣን ላይ ለመቆየትና የአገዛዙን በዘር ሐረግ የተዋቀረ የስልጣን ሽግግር ዘለዓለማዊ ለማድረግ ሲል በሚፈፅማቸው ከስብዕና የራቁ ተግባራትና የበቀል ወንጀሎች የተነሳ እጁ በንፁሐን ደም የጨቀየ ነው:: አገራችን በቀማኞች፣ በነፍሰ ገዳዬች፣ በነፃነት ጠላቶች፣ ዜጐችን በፍርሃት ሸብቦ፣ ሰብአዊ ክብርና አዋርዶ በችግርና በመከራ ቆፍድዶና አስጨንቆ ለዘለ ዓለም ለመግዛት ግጭቶችን በሚያቀጣጥል መከራ ተሰንጋ ተይዛለች:: ሕግና ሕግጋት መኖሩን ለመናገር የሚያስችል ተጠየቅ ስለሌለ አገዛዙ በጥይት ይገድላል፣ ቀጥቅጦ ይገድላል፣ አስሮና አሰቃይቶ ይገድላል፣ የዜጐችን ቤት ያፈርሳል፣ የአርሶ አደሩን መሬት ነጥቆ ይሸጣል፣ ሕዝብን ያፈላቅላል ሕግና ሕጋዊነት ሽታውም የለም ለአገዛዙ ሕግ ማለት ሐይል ነው:: አገዛዙ ለራሱ ዘር ብቻ ካልሆነ ለቀረው ደንታ የለውም:: የኢትዮጵያውያኖችን የተቃውሞ እንቅስቃሴ በቅርብ ሲከታተል የነበረው የአሜሪካ መንግሥት ከሰሞኑ ድንቁርናና ዕብደት በተቀላቀለበት መልክ ለወያኔ አገዛዝ ምስክርነቷን ሰጥታለች:: መግለጫውን አስመልክቶ የተለያዩ ትችቶች ሲሰነዘር ሰንብቷል:: የተቃዋሚው ወገን በወጉ የተሰላ የትግል አካሄድና ድርጅታዊ አቅሙም አመርቂ ደረጃ ላይ አለመገኝት ያስከተለው ሁኔታ የወያኔ ጌቶች ንቃታቸውን እያሳዩ መጥተዋል:: ይህ ንቀት አሜሪካኖች ብሔራዊ ጥቅማችን ብለው ከያዙት መርሆ ጋር የተያያዘ ነው:: በ 21 ኛው ክፍለ ዘመን የዲሞክራሲ ሻምፕዬን የምትባለው አሜሪካ በጉልበታም ስርአት የጭካኔ መዳፍ ውስጥ ገብተን በአንድ ዘር ወደአስከፊ ቀውስ እየተጓዝን መሆናችንን አያዩትም ለማለት አያስደፍርም:: ሚሊዮኖችን ረግጦ እየጨፈለቀ፣ አስሮ እያንገላታ ከሃገር እያሰደደና እየገደለ ለ25 ዓመታት መቆየቱን አላጡትም:: የሰሞኑን የድጋፍ ንግግር አደረገች የተባለችዋ የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚ/ር፣ ምክትል ሚኒስተር ዌንዲ ሸርመን ከሱዛን ራይዝ በአሁኑ ወቅት በተባበሩት መንግሥታት በአምባሳደር ደረጃ የአሜሪካ ተወካይ 3 ጋር በ80ኛዎቹ በሱዳን ተቀማጭነታቸውን አድርገው በጋዜጠኝነት እና በአሜሪካ የሰለላ ድርጅ (CIA ) ሲሰሩ ከፀረ ኢትዮጵያ ሐይሎች ጋር ማለትም ከወያኔና ሻቢአ ጋር የጠበቀ ግንኙነት የነበራቸው የዘመኑ ሹማምንቶች ናቸው:: እነዚህ ሁለት ሴቶች የአሜሪካ አስተዳደር ባለስልጣናት ለወያኔና ለሻቢአ ብዙ ውለታ የዋሉ ናቸው:: ሱዛን ራይስና ዊንዲ ሸርመን በ80ዎቹ በሱዳን እየተንሸራሸሩ የኢትዮጵያን አንድነት ከሚያጠፋ ሃይሎች ጋር በመሆን ሲያሻቸው ከሱዳን በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ሕወሐት የኰሚኒስትነት ካባውን ጥሎ አሜሪካ አድርግ የሚለውን ቢፈፀም ሥልጣኑ ወደእነሱ ሲተላለፍ እንደሚችል ያማለዱ ናቸው:: እንቀደሙት ጊዜያት ሁሉ የአሜሪካ የፅንፈኛነት የቀኝ አክራሪ ፖሊሲ የአገሮችን መብት ሲጋፋ የቆየ ነው:: በተለይም አሜሪካ ብቸኛዋ ልእለ ሃያል መንግሥት በመሆኗ በአለማችን ያላትን ተፅእኖ የምትገልፅበት መንገድ በንቀት ላይ ያረፈ ነው:: ዓላማዋን ያልተከተለ በወታደራዊ ጉልበቷ ታዳሽቃለች:: ወታደራዊ ቁመናዋ ማንም ሊጋፈጠው እንደማይችል ሙሉ ዕምነት ቢኖራትም በየአገሩ የደረሰባት መቀጣትና ውርደት ግን የሚናቅ አይደለም:: ዛሬ በየጊዜው ከዲክታተሮች ጋር በመሞዳሞድ ዓለምን ለመጋለብ የምታደርገው ሙከራ አላማችንን ወደ አልተረጋጋና የጥፋት ዘመን እያደረሰችን ነው:: አሜሪካኖች ወያኔን ዲሞክራቲክ መንግሥት ነው በሚል ሰርትፍኬት ሰጥተው አሸናፊ አድርገው የማውጣት ፍላጐታቸው የተያያዘው ወያኔን እንዳሻቸው ሊጋልቡት ስለሚችሉ ነው:: በሱማሊያ፣ በሱዳን፣ በምዕራብ አፍሪካ የተጫሩ እሳቶች ለማብረድ በምዕራባዊያን ትዕዛዝ ባምሳያው የፈጠረውን የጦርና የፀጥታ ሃይል በሕዝብ ለማዝመት ሳንጃውን ስሎ የሚንቀሳቀስ በመሆኑ ነው:: የአገሩን ዜጋ እየገደለ፣ እያፈነ፣ እያፈናቀለ በመከራና በስቃይ እያኖረ የተጫረ እሳት ለማጥፋት በዶላር ስጦታ ወዶዘማች የሚመለምለው ወያኔ ነው:: አሜሪካኖች በአህጉሩ እየተከሰተ ያለውን የቅራኔዎች መስፋፋት በማስቀጠል የስርዕት መናጋት በሚፈጠረው ሁኔታ ብሔራዊ ትቅማችን ያሉትን ለማስከበር የመረጡት የትግሬ/ወያኔን አገዛዝ ነው:: አሜሪካኖች ወያኔን አፍቅረንሃል ስላሉት የእልቂቱ ቀጠና አድርጐ የያዘው የከፋፍለህ ግዛ ቅራኔ ይባባሳል እንጂ አይበርድም:: በዚህ አቋማቸው እስከቀጠሉ ድረስ የዘለቄታ ብሔራዊ ጥቅም ያሉትን በወያኔ በኩል ለማስጠበቅ እንደማያስቸግራቸው መታወቅ ይኖርበታል:: የወያኔ እመቃ ዘለዓላማዊ አይደለም:: ሁላችንም እንደምናውቀው አሜሪካና እንግሊዝ በኬንያ አለሕዝብ ፈቃድ እያጭበረበረ በስልጣን ላይ ይቀመጥ የነበረው የአራፕ ሞይ አገዛዝ አቅፈውና ደግፈው ካቆዩት በኋላ በአመፅና በእንቢተኝነት ሊወገድ ችሏል:: የምዕራብ አገሮች ሕዝባዊ ቁጣ እስኪያዩ ድረስ በከፍተኛ የቅንጦት ደረጃ የተንደላቀቀ ህይወት እንዲኖሩ የሞራል የሚሊተሪና የፋይናንስ ድጋፍ በመስጠት አጉራ ዘለል አገዛዞች ዜጐቻቸውን ቀጥቅጠው እንዲገዙ ይፈቅዳሉ:: ዛሬ በአረቡ ዓለም የፈረሱትና ያሉት አገዛዞች የዚሁ የምዕራባውያን የብሔራዊ ጥቅም ውጤቶች ናቸው:: ምዕራባውያን መልካም አስተዳደር ግልፅነት እና ተጠያቂነት ያለው መንግሥት ይምጣ የሚሉት በሕዝባዊ ማእበል እንቅስቃሴ ሲተገበር ብቻ ነው:: የአገዛዙ በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠር የታጠቀ ሃይል ቢሰለፍ፣ እልፍ አእላፍ ፌርማቶሪዎች በሕዝብ መካከል ቢሰገሰጉ፣ ሚሊዮኖዎች ካድሬዎች ሃገር ምድሩን ቢያጥለቀልቁት የዘረኛው የትግሬ/ወያኔ አገዛዝ የፖለቲካ ክስረት እስካለ ድረስ ወሳኙ ጊዜ ነው:: የትኛውም ምድራዊ ሃይል ሊያመክነው የማይችል አብዬት መቀጣጠሉ አይቀሬ ነው:: ይህን ከታሪክ ማስታወሻ ጋር አያይዘን እንግለፅ:: የነጀነራል መንግሥቱ ነዋይ የታህሣሡ ግርግር እየተባለ በሚጠራው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ መክሸፍ ተከተሎ ጄኔራሉ ፍርድ ቤት በቀረቡበት ወቅት እንዲህ ብለው ነበር፣ 4 ዋ! ዋ! ዋ! ለእናንተም፣ (ለዳኞቹ ማለት ነው) ለገዢዎቻችሁ ጨመሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሃሳቤ በዝርዝር ገብቶት በአንድነት የሚነሳበት ጊዜ የሚደርስባችሁ መዓት የሚያሰቅቅ ይሆናል በሚል ተናግረው ለስቅላት በቅተዋል:: ያ ትንቢት ከ13 ዓመቶች በኋላ ከእጥፍ በላይ መፈፀሙን ስናስታውስ በጥቅመኝነት ስሌት ከስርዓቱ ጋር ተወዳጅተው የግፉአንን የመከራ ዕድሜ የሚያራዝሙ ሆድ አደሮችም ሆኑ የአገዛዙ ህሊቃን፣ ሕዝብ ””ሆ ”” ብሎ በአንድነት የተነሳ ዕለት ዶጋ አመድ መሆናቸው አይቀሬ ነው:: ለነገሩ ይዘግይ እንጅ ታሪክ በእውነት እንጅ ከፍረሃት ጋር ውል ኖሯት አያውቅም:: በዘውግ ማንነት ማለፍ ግድ የሆነባት አገር፣ የወፍን ያህል የራስ ጐጆ መመኘት እንኳን እንደ ህብሰተ መና በራቀበት ምድር፣ ዜጐች በምርኰኛ ሕግ ተቀፍድደው ውለው በሚያድሩበት ክልል፣ መማር ድንጋይ ከመፍለጥ በማያሸጋገርበት ዘመን የመኖርና ያለመኖር ግድግዳው ጣራው ተደርምሶ ሁሉም ነገር ከንቱ በሆነበት አገር ዝምታው መጥፊያችን ሆኗል:: አጋሮቻቸውም ሞትን በይነውብናል :: ስለሆነም ትግላችን የአሜሪካንን ላይሰንስ አይጠይቅም:: ጭቆና፣ በደል፣ ግፍ አለብን ካልን፣ የማሸነፊያ ብቸኛ መንገድ የፍርሃትን ሰንሰለት ሰባብሮ በዘረኞች ፍቃድ ለቆመው ስርአትም ሆነ በድምፅ አልባ ተወካይዎች አጃቢነት ለፀደቁት ሕግጋት አለመታዘዝን በፊት ለፊት ስናስተጋባ ብቻ ነው:: በእምቢተኝነት ደም አልባ ሰላማዊ አመፅ የገዥዎችን ሰፈር ስናርበደብድ ብቻ ነው:: አደባባይዎችን በሰው ጐርፍ ማጥለቅለቅ ስንችል ብቻ ነው:: ለመብታችን፣ ለነፃነታችን፣ ለክብራችን እስኪንበረከኩ ድረስ በትግል በፅናት በመቆም ቁርጠኝነታችንን ስናሳይ ነው:: የትውልድና የአገር ደዌዎችን የምንገላገለው ሰፊና ቆራጥ ሕዝባዊ ሃይል ወደ አደባባይ ስናወጣ ብቻ ነው:: ይህ ሲሆን ብቻ ነው የወያኔ ሸሪኰች እጃቸውን የሚሰበስቡት::                                                                                                                                                                      ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ! ከስቶክሆልም ስዊድን

Friday, May 1, 2015

From Poet Getnet for Ethiopians In Libya! ገጣሚ አቶ ጌትነት እንየው በሚዘገንን ሁኔታ ውድ ሕይወታቸውን ሊቢያ ላይ ለአጡት ኢትዮጵያውያን የተገጠመ ነው።

 
ሞት ሆነ ፋንታችን የእኛስ በዓለም ላይ፣
ጠላት እያጠቃን፤ስለማንመክት ነው የምናይ ስቃይ።
ስለዚህ፦ መፍትሄ ሚሆነው በግልፅ የሚታየው፣
ቆራጥ ጀግና ሁኖ በአንድ ላይ ማበር ነው።
አጊላ ኢትዮጵያ ሁሌ የሚለው፣
አንድነት ግዴታ ብሎ ሚጣራው፣
ስለተረዳ ነው የድልን መምጫው።
የግድ ነው ቆርጦ መነሳት፣
ያለዚያ! ዘላለም እለቅሶ መጨረሻው ሞት።

Logo.png
አምላክ ይዘን!
ኢትዮጵያ እማማ አይዞሽ
አለን ቁመናል ልጆችሽ
እንዳይጠፋ ክቡር ገፅሽ
በመመከት ከጠላትሽ
ከሚጥሩት ሊበትኑሽ
አከላትሽን ከሚቆርጡሽ
ከተገዙት ለሹምባሽ
አባቶች እንዳቆዩሽ
ገድለውና ሙተውልሽ
ከትውልድ ትውልድ እዳዳኑሽ
እኛም አንሁንም ተውቃሽ
እንሆናለን ፈጥኖ ደራሽ
አምላክን ይዘን በዙሪያሽ
እንታገላለን ልናቆይሽ
ዘላለማዊ ህይወት እንዲኖርሽ
ኢትዮጵያ ወይንም ሞት ብለንልሽ
አጊላ ኢትዮጵያ ፈጥረንልሽ
አንድነት ግዴታ እያልንልሽ
ነሳን ልጆችሽ፣ ተነሳን ልጆችሽ።