ከወያኔ ጋር በምርጫ ለመካፈል ለምን ፈለጋችሁ ? ምንስ ለመሆን ነው?
በምርጫ ከወያኔ ጋር መካፈል የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ወይንም የሰላም ትግል መፍትሄ አይደለም።የወያኔ
ሥርዓት በዓይነቱ ምርጫዊ አምባገነንነት በምርጫ ዴሞክራሲያዊ ሽፋን ያለው፤ የለየለት ፋሽስት አምባገነን
ሥርዓት ነው። እምቢተኛና ኃይልን የሚጠቀም ሕግ የማያውቅ የሽፍታ ቡድን ማፍያ ነው። ወያኔ
ያልተቆጣጠረው፤ ወያኔ የበላይ አስተዳዳሪ አለቃ ካልሆነ ዴሞክራሲ የለም ብሎ የሚያምንና ዓላማውን
በዚህ ሽፋን የአገር ማፍረስን፣ የአገር ሃብት ዘረፋውን፣ሕዝብ የማሰቃየት ተግባርን ሥራ ላይ የሚያውለው
ወያኔ ብቻ በሥልጣን በወያኔዊ መንግሥት ሲኖር ነው ብሎ የሚያስብና የወሰነ ነው።
ይህን ያቀደና ዓልሞ የተነሳ በመሆኑም በሥልጣን ላይ ያለው የወያኔ መንግሥት ማንኛውንም ዓይነት
ስልትና ተንኰል፣ኃይልና እምቢታን መግደል ፣ ማሰር ፣ማሳደድን፥ ከዚያም በተቃዋሚ ድርጅቶች ውስጥ
ሰርጐ በመግባት ቀፎ አድርጐ እየተጠቀመና አምክኖ በማጥፋት፤ ወያኔ እሱ ብቻ እንዲያሸንፍ ያደርጋል።
ወያኔ በተፈጥሮው ሽፍታ እምቢታ፣አመጽ፣ሃሰት ባህሪው ወያኔዊ ስለሆነ የተቃወመውን ሁሉ በማሰርና
በመግደል ያጠፋል። በደም ትግል የተገኘ ሥልጣን ነው ብሎ ስለሚያምን ያለ ደም መልቀቅ አያስብም።
ወያኔ ሕገ ወጥ፣ እምቢተኛ ሽፍታ፣ ፈሪሃ እግዚአብሔር የሌለው፤ዓላማው የአገር ጥፋትና ዘረፋ ነው።
በሕዝብ ላይ ያለው ንቀትና ማን አለብኝነት ፀረ አገር፣ ፀረ ኅብረተሰብ የሆነ የወጣለት የአገር ጠላት
ነው።ወያኔ በምርጫ ሽፋን ኃይልን ተጠቅሞና አስገድዶ እንደ ልማዱ አሸነፍኩ ብሎ በምርጫዊ
አምባገነንነቱ ሥልጣን ላይ ለመቆየት ምርጫን በሞኖፖሊ ስልት አድርጐ ያለ እንጂ፣ በሕዝብ ተወድዶ
ለመመረጥ አይደለም።
ይህን ካልንና ከተረዳን ፤ የአንድ አገር ሕዝብ መንግሥት ፤ ሕግና ሥርዓት ኖሮት ያን ሕግ ሕዝብ አክብሮ
መኖር ሰላምና ደህንነት፤የነፃነት መብትም ግደታም ነው። ነገር ግን አገርን እንደ አገር፤ ሕዝብንም እንደ
ሕዝብ፤ ወገኔ የማይል የማይወድና የማያከብር፣ የሚንቅ፣የሚያዋርድ፣የሚያሰቃይና የሚያጠፋ በሕገ ወጥ፤ ሕግ የሚመራ ፍጹም ፋሽስታዊ ወራሪ ወያኔዊ የኃይል መንግሥት ብሎ መኖር አይቻልም።ነፃነት
የጐደለው፣ዜግነት የተቀማበት፣ስብዕና ያነሰው፣መብት የታጣበት በመሆኑ ሕዝብ ይህን ዓይነት ሕግ እንደ
ሕግ የበላይነት አይቶ አይቀበልም።በመሆኑም ሕዝብ ይህን ዓይነት ሕግና ሥርዓት አምርሮ በመታገል
የዜግነት መብትና የነፃነት ክብሩን ማስከበር የተፈጥሮ የሰው ልጅች የመኖር መፍትሄና ተፈጥሮዊ ባህሪና
ግደታ ነው።
በባንዳ ወያኔ እየተገዙ የአገር ሉዓላዊነትን፣የዜግነት መብትን ተነፍጐ፣ መሬት አልባና ሃብት እየተነጠቁ
ኢትዮጵያ ፣ ኢትዮጵያዊነትና ሰንደቅ ዓላማችን ተደፍረውና ተዋርደው ይገኛሉ። ተቃዋሚዎች ይህን
እየተረዱና እያወቁ በትዕግሥትና በችልታ መመልከት የሞት ሞት ሲሆን ኢትዮጵያዊ ፀባይና ባህሪም
አይሆንም። የወያኔን አረመኔ ባንዳነት ከተገነዘቡና ከተረዱ ወያኔን እንደ ዴሞክራሲዊ አገራዊ ፓርቲ
ተቀብሎ ምርጫ ውስጥ መግባትና መካፈል፤ ለወያኔ አመኔዊ ሥርዓት መንግሥቴ ብሎ እውቅና መስጠት ከመሆኑም በላይ አገርና ሕዝብን አሳልፎ ለከፋ ጥፋት ማስረከብ ነው። ወያኔ አገርና ሕዝብ እያጠፋ ያለ
ፀረ ሕዝብ ጠላት ሆኖ የሚቀጥል እንጂ፤በምርጫ ተሸንፎ እንደ ሚወጣና አሸናፊውንም በሰላም ተቀብሎ
የሚለቅ አይደለም። እንዳውም ወደ ከፋ ብጥብጥ ፣ማስር፣ ግድያና ፣ ደም ማፍሰስ ውስጥ የሚገባ ሕግ
የማያውቅና የማያከብር ኢሰብዓዊ አረመኔ ሽፍታ ቡድን ነው። ይህን ጨካኝ አምባገነን ሥርዓት በምርጫ
ሁኔታ አጅቦ በጭፍራነት አብሮ መጓዝ ሳይሆን ታግሎ ማሸነፍና ማስወገድ ነው።
ተቃዋሚ ማለት ወያኔና ሥርዓቱን ገርስሶና ጠራርጐ በመጣል፤ ኢትዮጵያን አድኖ፤ የሕዝብ የበላይነትን
ማረጋገጥ ማለት ነው።ይህን ለማድረግ በቁርጠኝነት ለመሰዋዕትነት መዘጋጀትና መሳተፍን ይጠይቃል።
በቁርጠኝነትና በፅናት ለመሰዋዕት ይህን ወቅታዊ ትግል ያልተረዳ ትግል የትም አያደርስም። ማንኛውም
ፀረ ወያኔ ትግል፦ የወያኔ ያገር ጠላትነት ከተረዳ ትግሉ የነፃነት፣ ከሕይወት እስከ ሞት ድረስ መስዋዕትነትን
የሚጠይቅ ነው። ለዚህ በቁርጠኝነት የመሰዋዕትነት ዝግጅት የሌለው ትግል በቀዘቀዘ ወኔ፣ በፈሰሰ አሞት
በተቃዋሚነት እያፈገፈጉ ማቅራራትና ዘራፍ! ምርጫ እያሉ አብሮ መዋል የሕዝብ ብሶትና ጩኽትን
አይወጣም፤ የትም የማያደርስ ለማንም ለራስ ለአገርም አይሆንም።
የወያኔ ሕገ መንግሥትን እናውቃለን፣ይከበርልን፣ሥርዓቱን እንቀበላለን በእዚህ ውስጥ የወያኔ ሕግ
በሚፈቅደው መሰረት እንሳተፋለን የሚሉ ከሆነ አፍቃሪ ወያኔ ድርጊታቸው የሚጠቅመው ወያኔን ብቻ
እንደሆነ ተገንዝበው በምርጫ ይሳተፋሉ። ነገር ግን አይ እኛ በቃን የወያኔ ሕልውና፣ሕገ መንግሥትና
ሥርዓት አገርና ሕዝባችንን ጐድቶብናል የሚሉ ከሆነ ደግሞ በምርጫ መካፈል አይኖርባቸው ምርጫው
የነርሱ ነው።ከታሪካዊ ስተታቸው ሳይማሩ፤ ሽንፈትን ተከናንበው ዛሬም እንዳለፈው ለመሳተፍ ማቀድ
የወያኔን ባህሪና የሽፋን ዴሞክራሲውን ያልተሩዱ፣ የፖለቲካ ንቅዘቱን መተቸት ብቻ ጥሩ የሰሩ
የሚመስላቸው የፖለቲካ ግንዛቤያቸው ዝቅ ያለ ያደርገዋል። ሕዝብ እየጠየቀ ያለው፤ የወያኔን ሸፍጥ አለመረዳት፣ደካማ፣ ተላላና ዝንጉ ሆነን አገርና ሕዝብ ተጐዳ ነው።
ወያኔ ይወገድልን የሰው ፣ ያገር ያለህ ኢትዮጵያን እናድን፣ ከባንዳ ጭፍጨፋና ዘረፋ ነፃ እንሁን ነው።
ወያኔና ሥርዓቱን በተባበረ በሕዝብ ኃይል እንገርስስ ነው።
ስለዚህ አገር ውስጥ ያሉ ድርጅቶች ኢትዮጵያን ከወያኔ ለማዳን የሚፈልጉ ከሆነ ትክክለኛ አቋምና የትግል
ስልት መከተል አለባቸው።ትግሉ የሚጠቀው ወያኔና ሥርዓቱን በሕዝብ አመጽ ገፍትሮ መገርሰስና መጣል
እንጂ በብሔራዊ ምርጫ ተቻችሎና ተለማምጦ ከወያኔ በምርጫ ድለላ የሚሰጥ ወንበርን ተስፋ ማድረግን
አይደለም። ወያኔና ሥርዓቱን ለመገርሰስ የሚቻለው በሕዝብ አመጽ ነው። አመጽ ደግሞ ቁርጠኝነትን፣
አልበገርነትን፣ መስዋዕትነትንና ያለማቋረጥ ታግሎ ማሸነፍን ይጠይቃል።ሕዝብ እየጠየቀ ያለው ወያኔ
ይወገድልን ነው።ወያኔንም መንግሎ የሚጥለው የሕዝብ አመጽ ነው።ሁኔታው የሚጠይቀውን ከሕዝብ
ጋር የሚመጥን አማራጭ የትግል ስልት መቅረጽና መከተል ያስፈልጋል።ይህን አውቆ መነሳት ሕዝብን
ማደራጀት፣ ማንቃትና አቅጣጫ በመስጠት መምራት አማራጭ የሌለው ወቅቱ የሚጠይቀው የትግል
ምዕራፍ ነው።ሰለሆነም በሕዝብ መሃከል በመዋል ፍርሃትን ተቆጣጥሮ ሕዝብን ይዞ ለአመጽ መዘጋጀት
ነው።ከዚህ ያነሰ የትግል ይዘት የውሸት ከወያኔ ጋር ምርጫ መካፈልን ትቶ በሕዝባዊ አመጽ ወያኔን
ማስወገድና የኢትዮጵያን ትንሳኤ ማረጋገጥ ነው።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ ! ! ! የካቲት 2/2007
The Patriotic Ethiopians for Ethiopian Unity! To Liberate Ethiopia from Shabia Woyane! ኢትዮጵያውያንን በማስተባበር፤ ኢትዮጵያንና ደጉን ሕዝብ ከሻቢያ ወያኔ ነፃ ለማውጣት የሚፋለም ነው! እውነት! እምነት! ጽናት! www.agillaethiopia.blogspot.com Contact us: tefalemjegna247@gmail.com ጎጠኝነት! ተንኮል! ምቀኝነት! ክፋት! ውሸት ጠላቶቻችን ናቸው!!! በዓለም ተበትኖ ዘላለም ከማልቀስ፣ ክንድን አጠንክሮ ጠላትን መደምሰስ! ተነስ! ተነሽ!
WAO- We All One! Ethiopians!
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment
Note: Only a member of this blog may post a comment.