ከመሰደድ ይልቅ ደፍሬ ቆረጡሁ፣
ውስጥ ውስጡን ወገኔን እያነቃቃሁ፣
በሚቻለው ሁሉ ልፋለም ወሰንሁ፣
ጎጠኛን ባንዳውን እየጠራረግሁ።
ባዕዳን ወራሪው ከአገር እንዲወጣ፣
እንደ ድሮው ሁሉ ትውልድ እንዲቆጣ፣
መሰደድ አቁሞ ጠላት እንዲቀጣ።
ውጭ ማምለኩን ትቶ እንዲቆም ለአገር፣
ኢትዮጵያን በማጣት ዓለም ከሚዞር፣
ይሁን የአንቺ መዝሙር ወገን እንዲደፍር።
ክንድን ማጠናከር በሁሉም መስመር፣
የግድ ያስፈልጋል ያለ ጥርጥር፣
አገር የለሽ ሁነን ጠፍተን እንዳንቀር።
No comments:
Post a Comment
Note: Only a member of this blog may post a comment.