ቆራጡ ጀግናው፣
ለአገር የቆመው፣
በዓላማው የፀና እስከ ፍፃሜው።
በእናት አገር ጥቃት ልቡ የቆሰለ፣
በትግል ተጠማጅ መናኝ የመሰለ፣
ይገፋል አይቆምም ከአላስተካከለ።
ምንም ማይናገር ፍፁም ማያወራ፣
ራአዩን ውጥኑን የሚያሳይ በስራ፣
ይህ ነው ቆራጡ የኢትዮጵያ አውራ።
ሥራው ታምረኛ ጥበቡ ረቂቅ፣
ወገንን አስደሳች ጠላት ሚያስጨንቅ።
በዓለም አቀፍ ዙሪያ ጀግናን አሰማርቶ፣
ቆራጥ አያይዞ ሰንሰለቱን ሰርቶ፣
ኢትዮጵያን ሊያድን ነው ወያኔን ፈንክቶ።
ምን ትናገር ይሆን አሳባቂ ሁሉ፣
ጀግና እየገፋ ነው በዱር በገደሉ።
በአገር ውስጥም ከውጭም ባለው፣
ጀግና ታያይዟል ጠላት ይጭነቀው።
ወረኛም ያወራል፣
ጀግና ይሰማራል፣
ጠላትን ይሰብራል።
ኢትዮጵያ ገናና ብሎ ይዘምራል፣
እንደ ድሮው ሁሉ አገር ያስክብራል።
ለአገር የቆመው፣
በዓላማው የፀና እስከ ፍፃሜው።
በእናት አገር ጥቃት ልቡ የቆሰለ፣
በትግል ተጠማጅ መናኝ የመሰለ፣
ይገፋል አይቆምም ከአላስተካከለ።
ምንም ማይናገር ፍፁም ማያወራ፣
ራአዩን ውጥኑን የሚያሳይ በስራ፣
ይህ ነው ቆራጡ የኢትዮጵያ አውራ።
ሥራው ታምረኛ ጥበቡ ረቂቅ፣
ወገንን አስደሳች ጠላት ሚያስጨንቅ።
በዓለም አቀፍ ዙሪያ ጀግናን አሰማርቶ፣
ቆራጥ አያይዞ ሰንሰለቱን ሰርቶ፣
ኢትዮጵያን ሊያድን ነው ወያኔን ፈንክቶ።
ምን ትናገር ይሆን አሳባቂ ሁሉ፣
ጀግና እየገፋ ነው በዱር በገደሉ።
በአገር ውስጥም ከውጭም ባለው፣
ጀግና ታያይዟል ጠላት ይጭነቀው።
ወረኛም ያወራል፣
ጀግና ይሰማራል፣
ጠላትን ይሰብራል።
ኢትዮጵያ ገናና ብሎ ይዘምራል፣
እንደ ድሮው ሁሉ አገር ያስክብራል።
No comments:
Post a Comment
Note: Only a member of this blog may post a comment.