WAO- We All One! Ethiopians!

WAO- We All One! Ethiopians!

Wednesday, October 22, 2014

The Program of Agilla Ethiopia (የአጊላ ኢትዮጵያ መለስተኛ ፕሮግራም። )






የአጊላ  ኢትዮጵያ የነፃነት ትግል መመሪያ
ክፍል 1
የአጊላ  ኢትዮጵያ ራዕይ፣ ተልኮና ግቡ።
ራዕይ_ዲሞክራቲክ  ስር ዓት መገንባት ነው።
ተልዕኮ፣  የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ን ልጆች በአገርም ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ዙሪያ ለነፃነት ትግል ማሰባሰብና ማደረጀት ነው።
         የሕግ የበላይነት እንዲከበር፣ የኢትዮጵያ ዳር ድንበር እንዲጠበቅ፣ የሕዝቡም  አንድነት እንዲረጋገጥ ጠንክሮ
         ይታገላል። ይህም ተግራባዊ እንዲሆን ነፃነት፣ሰላም፣እኩልነት በአጠቃላይ የግለሰቦች መብት የሚከበርባትና ውነተኛ ምርጫ የሚደረግበት
          እንዲመጣ ታግሎ ያታግላል።
ዓላማ፣   ደከመኝ ሳይል  ሌት ከቀን በመስራት የሻቢያን ወያኔ ፋሽስታዊ ጠላት ታግሎ ማስወገድ ነው።
          ህ. የኢትዮጵያ ሕዝብ ለኢኮኖሚ፣ ለፖለቲካ፣ ለማሕበራዊ ለውጥ በማዘጋጀት ከግፈኛው የሻቢያ ወያኔ ጎጠኛ ቡድን  ቀንበር  ለማውጣት
               የነፃነት ትግል ተሳትፎ እንዲያደርግ ታግሎ የሚያታግል ነው።
           ለ.የትግሉ ሂደት እንዲሳካ፣ ለነፃነት ትግሉ ኢትዮጵያውያንን በማረባረብ  የቁሳቁስ፣ የገንዘብ፣ ማነኛውንም የሀይል ምንጭ ከአባላትም ሆነ
               ከህዝቡ በማሰባሰብ የትግሉን ንቅናቄ በመለኮስ፣ በማፋፋምና በማስፋት ችሎታ ያላቸውና ጠንካራ የሆኑ የመሪዎች አስፈላጊነትን 
               በመገንዘብ እስከ ሕይወት መስዋዕትነት ለመክፈል በማዘጋጀት የተሳካ ትግል በማድረግ ዲሞክራቲክ መሰረት መጣል ነው።
           ሐ.የመርዘኛውን የሻቢያ ወያኔን ቆሻሻ በማጽዳት ለአንዴም ለመጨረሻም በመጥረግ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የድል ውጤት ማስጨበጥ ነው።
ግብ፣        የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ የሕዝቡን አንድነት፣ ነፃነት፣ ሰላም የሚያረጋግ ጥ  በሕዝብ የተመረጠ  ለሕዝብ የሚሰራ ስርዓት መፍጠር ነው።     
      

No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.