መሬት ያለ እናት፣
መሬት ያለ መብት፣
መሬት ያለ መብት፣
አለሁ የማለት፣
የባዶው ሕይወት፣
የቁም ጣረሞት፣
እያወቁ ሞት።
ኢትዮጵያዊ ፍጡር፣
ያለህ ካለመሬት ምድር።
መሬት እያስወረስህ፣
በቁም የጠፋህ፣
በአየር ላይ የተንሳፈፍህ።
ወሬ የምታወራ፣
በባዶው የምታቅራራ፣
ስራ ግን የማትሰራ።
የሌለህ መሰረት፣
የምትናቆረው ባለፈው ሕይወት፣
የድሮውን በአያት ጊዜ፣
ምነው የአሁን ዋይ ዋይታው ኑዛዜ።
አሁን ምትከፉ፣
መላውን ማትነድፉ፣
በጋራ ማትለፉ፣
በመነጣጠል አንድ በአንድ ምትጠፉ።
አሳዘነኝ ወገን የኢትዮጵያ ልጅ፣
ጥሪ ላቅርብለት ቶሎ እንዲደራጅ፣
በአጊላ ኢትዮጵያ ለአንድነት ግዳጅ፣
እየገፋ መጥቷል እያሰማ አዋጅ።
እርቁን ይፍጠርና ቁሞ መፋጀት፣
ኢትዮጵያን ይጠብቅ ከእጁ እንዳያጣት።
በእናት አገር ላይ፣
ዋ! እንዳይመጣ ስቃይ።
መጤው ከላይ ወጥቶ፣
ነባሩ ተነጥቆ፣
እንደ ተቀጥላው እንደ ሚመጠው፣
ሐረግ መስሎ ገብቶ እንደ ሚነጥቀው፣
ዋናውን አጥፍቶ እንደሚነግሰው።
እንዳይሁን በኃላ አሁን ፈራሁኝ፣
ለአንድነቱ ብየ ይቅር ከአላልሁኝ።
እንዳይሆን መራር የከፋ ሀዘኑ፣
ታየኝ ሚደገሰው የጥፋቱ ቀኑ።
No comments:
Post a Comment
Note: Only a member of this blog may post a comment.